ዕብራዉያን ፲፫:፲፫-፳፪

፲፫ አሁንም ፡ ወደ፡ እሱ ፡ ከከተማው ፡ እንውጣ ፤ ተግዳሮቱን ፡ ተሸክመን ። ፲፬ እዚህ ፡ የሚኖር ፡ አገር ፡ ያለን ፡ አይደለም ፤ የምትመጣውን ፡ እንሻለን፡ እንጂ ። ፲፭ እንግዲህ ፡ በየጊዜው፡ ለእግዚአብሔር፡ የምስጋና፡ መሥዋዕትን፡ ልናቀርብ፡ አይገባንምን፤ የከንፈሮቻችንን፡ ፍሬ፤ በስሙ፡ እናምን ፡ ዘንድ ። ፲፮ ለድሆች መራራትን ከነሱ ጋር መተባበርን አትርሱ ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና ። ፲፯ ለመምሮቻችሁ ፡ ታዘዙ ፤ ተገዙላቸው ፤ እነሱ፡ ስለ፡ነፍሳችሁ ፡ ያስባሉና ፤ በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ስለ፡እናንተ፡ የሚተሳሰቡአቸው ፡ እንደ፡ መሆናቸው ፡ መጠን ፤ ይህን ፡ ደስ ፡ ብሎአቸው ፡ ያደርጉት ፡ ዘንድ ፤ ሳያዝኑ ። ፲፰ ይሀም፡ ይገባችጉአል ፤ ስለ ፡ እኛ ፡ ትጸልዩ ፡ ዘንድ ፤ ለሁሉ ፡መልካም ፡ ነገርን፡ እንደምትወዱና ፡ እንደምትሹ ፡ እናምናለን፡፡ ፲፱ የበለጠውንም፡ ይህን፡ታደርጉ፡ ዘንድ ፡እማልዳችኁአለሁ ፤ ፈጥኜ ፡ እደርስላችሁ ፡ ዘንድ ። የበጎችን ፡ እረኞች፡ አለቃ ፡ ከሙታን ፡ ያስነሣው ፡ የሰላም፡ አምላክ ፡ ዘለዓለም ፡ የሥርዐት ፡ ደም፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስን ፡ ለማገልገል ፤ በፍጹም ፡ በጎ ፡ ምግባር ፡ ፈቃዱን ፡ እንድታደርጉ ፡ ያጽናችሁ ። ፳፩ እሱ ፡ የሚወደውን ፡ እየሠራላችሁ ፡በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ክብር ፡ ምስጋና ፡ ገንዘቡ ፡ የሚሆን ፡ ለዘለዓለም ፡ አሜን ።