ሉቃስ ፪:፴፰-፵

፴፰ ያንጊዜም ተነሥታ አመነች ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ፤ የኢየሩሳሌምን ድኅነት ተስፋ ለሚያደርጉ ሁሉም የእርሱን ነገር ተናገረች ። ፴፱ በእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈውን ከፈጸሙ በኋላ ወደ ገሊላ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት ተመለሱ ። ሕፃኑ አደገ ፤ በዕውቀትም ጸና ፤ ጥበብንም የተመላ ነበር ፤ ባለው በእግዚአብሔር ጸጋ ፍጹም ነበር ።