ያዕቆብ ፬:፲፩-፲፯

፲፩ ወንድሞቻችን ! እርስ ፡ በርሳችሁ ፡ አትተማሙ ፤ ወንድሙን ፡ የሚያማ ፡ የሚነቅፈውም ፡ የእግዚአብሔርን፡ ሕግ፡ ያማልና ፤ የእግዚአብሔርንም፡ ሕግ ፡ ይነቅፋልና ፡ ሕጉን፡ የምትነቅፍ ፡ ከሆንክ ፡ ደግሞ ፡ ፈጻሜ ፡ ሕግ ፡ አይደለህም ፤ ሕግ ፡ አፍራሽ ፡ ሆንክ ፡ እንጂ። ፲፪ ሕግን ፡ የሠራ ፡ የሕግ ፡ ባለቤት ፡ አንድ ፡ ነውና ፤ ማዳንም ፡ መግደልም ፡ የሚቻለው ፡ እሱ ፡ ነው ፤ እንግዲህ ፡ ባልንጀራህን፡ የምትነቅፈው፡ አንተ፡ ምንድነህ። ፲፫ ዛሬ፡ ወይም፡ ነገ፡ ወደዚያች፡ አገር፡ እንሔዳለን፤ ከዚያ፡ እንኖራለን፤ እንሠራለን ፤ እንጠቀማለን ፤ እንደሚሉ ፡ ነገ ፡ የሚሆነውን ፡ እንደማያውቁ ። ፲፬ ሕይወታችሁ ፡ ምንድነው ፤ እናንተማ ፡ ላንድ ፡ ጊዜ ፡ ታይቶ ፡ ኋላ፡ እንደሚጠፋ ፡ እንደ፡ ጢስ ፡ አይደላችሁምን ? ፲፭ እግዚአብሔር ፡ ቢፈቅድና ፡ ብንኖር ፡ ይህን ፡ ወይም ፡ ያን ፡ እናደርጋለን ፡ በማለት ፡ ፈንታ ። ፲፮ ሁን ፡እናንተ፡ በሥራችሁ፡ ትመካላችሁ ፤ እንደዚች ፡ ያለችው ፡ ትምክሕት ፡ ሁላ ፡ ክፉ ፡ ናት ። ፲፯ በጎ ፡ ነገር ፡ ማድረግን ፡ የሚያውቅ ፡ የማይሠራትም ፡ ኃጢአት ፡ ትሆንበታለች ።