የሐዋርያት ሥራ ፳፭:፲፩-፳፩

፲፩ ከበደልኩ ለሞት የሚያበቃኝ የሠራሁት ክፉ ሥራ ካለም ሞት አይፈረድብኝ አልልም ፤ በደል የሌለኝን እሊህ በከንቱ የሚከስሱኝ ከሆነ ግን ፤ ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ ለማን ይቻለዋል ፤ እኔ ወደ ንጉሥ ቄሣር ይግባኝ ብያለሁ ። ፲፫ ጥቂት ፡ ቀን፡ በኋላም፡ንጉሥ፡ አግሪጳና ፡ በርኒቄ ፡ ወደ፡ ቂሣርያ ፡ ወርደው ፡ ፊስጦስን ፡ ተገናኙት ። ፲፬ ከርሱ ፡ ዘንድም ፡ ብዙ ፡ ቀን፡ ከቆዩ ፥ በኋላ ፥ የጳውሎስን ፡ ነገር ፡ ነገራቸው ፤ እንዲህም ፡ አላቸው ፤ ፊልክስ ፡ በእስር ፡ ቤት ፡ ትቶት ፡ የሔደ ፡ አንድ ፡ እስረኛ ፡ ሰው ፡ አለ። ፲፭ ኢየሩሳሌም ፡ ሳለሁ ፡ የካህናት ፤ አለቆችና ፡ የአይሁድ ፡ ሽማግሌዎች ፡ ወደኔ ፡ መጥተው ፡ ለእነሱ፡ ብዬ ፡ እንድፈርድበት ፡ ማለዱኝ ። ፲፮ አይሆንም ፤ ሕግም ፡ የለም፤ ምስክር ፡ ያልጮኸበትን፡ በደል ፡ ያልተገኘበትን፡ ለመቅጣት፡ የሮም ፡ ሰዎች ፡ ሰውን ፡ እንዳገኙ ፡ አይገድሉም፤ የተከለከለ፡ ነው፡ አልኩአቸው። ፲፯ ከዚህ ፡ በኋላ ፤ ወደዚህ ፡ በመጣሁ ፡ ጊዜ ፡ ዳግመኛ ፡ ተሰበሰቡ ፤ በማለዳም ፡ ከዐደባባይ ፡ ተገኘሁላቸው ፤ ያንን ፡ ሰውም ፡ እንዲያመጡት ፡ አዘዝኩ ። ፲፰ የከሰሱትንም፡ ከእሱ ፡ ጋር ፡ አጋጠምኩአቸው ፤ ግን ፡ እንደ ፡ አስብኩት ፡በከሰሱት፡ ክስ፡ የሠራው፡ ምንም ፡ነገር ፡ የለም ። ፲፱ ከሚከራከሩበት ፡ ከሕጋቸው፡ በቀር ፤ ኢየሱስ ፡ የሚባል ፡ አንድ፡ ሰው ፡ አለ፤ ሞቶአል፡ ጳውሎስ ፡ግን፣ ተነሥቶአል፡ ይላል፡፡ ስለ ፡ ክርክራቸውም ፡ የማደርገውን ፡ አጥቼ ፣ ጳውሎስን፡ ወደ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ሔደህ ፡ በዚያ ፡ ልትከራከር ፡ ትወዳለህን ፡ አልኩት ። ፳፩ እርሱ ፡ ግን ፥ እንቢ ፡ አለ ፤ ከሞት፡ መዳኛውንም፡ ወደ፡ንጉሥ፡ተማጠነ ፤ ከዚህም ፡ በኋላ ፡ ወደ፣ ቄሣር፣ እስክልከው ፡ድረስ ፡ እንዲጠብቁት ፣ አዘዝኩ ።