ዮሐንስ ፰:፫-፲፪

ቅዳሴ: የሠለስቱ ምእት

የሚዘከሩ ጻድቃን ሰማዕታት: አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ አባ ዲር ወኤራኢ ወሶስና ቅድስት ወካልአን ሰማዕት

ሙሉዉን ንባብ ያንብቡ




ያዕቆብ ፬:፲፩-፲፯

፲፩ ወንድሞቻችን ! እርስ ፡ በርሳችሁ ፡ አትተማሙ ፤ ወንድሙን ፡ የሚያማ ፡ የሚነቅፈውም ፡ የእግዚአብሔርን፡ ሕግ፡ ያማልና ፤ የእግዚአብሔርንም፡ ሕግ ፡ ይነቅፋልና ፡ ሕጉን፡ የምትነቅፍ ፡ ከሆንክ ፡ ደግሞ ፡ ፈጻሜ ፡ ሕግ ፡ አይደለህም ፤ ሕግ ፡ አፍራሽ ፡ ሆንክ ፡ እንጂ። ፲፪ ሕግን ፡ የሠራ ፡ የሕግ ፡ ባለቤት ፡ አንድ ፡ ነውና ፤ ማዳንም ፡ መግደልም ፡ የሚቻለው ፡ እሱ ፡ ነው ፤ እንግዲህ ፡ ባልንጀራህን፡ የምትነቅፈው፡ አንተ፡ ምንድነህ።