ማቴዎስ ፲፪:፴፰-፵፪

ቅዳሴ: የጌታ

በዓል: ነነዌ

፴፰ ያን ጊዜም ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ሰዎች መጥተው ፤መምህር ! ካንተ ምልክት ልናይ እንወዳለን አሉት ። ፴፱ ጌታ ኢየሱስም መልሶ ከዳተኛዪቱ ፤ ዐመፀኛዪቱ ፤ አመንዝራዪቱ ትውልድ ምልክት ትሻለች ፤ ምልክቱ ግን አይሰጣትም ፤ ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ።

ሙሉዉን ንባብ ያንብቡ

መዝሙረ ዳዊት ፪:፲፪

፲፪ ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።



ያዕቆብ ፭:፩-፲

አሁንም ፡ እናንተ፡ ባለጠጎች ፡ ኑ ፤ በምትመጣባችሁ፡ በጕስቍልናችሁ፡ ምክንያትም ፡ እየጮኻችሁ፡ አልቅሱ ። ሀብታችሁ ፡ ነቀዘ ፤ ልብሳችሁንም ፡ ብል ፡ በላው ።