ሉቃስ ፰:፩-፳፪

ቅዳሴ: የኤጲፋንዮስ

ከዚህም በኋላ በማግሥቱ ጌታ ኢየሱስ በየአገሩ በየመንደሩ ተመላለሰ ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥትም ሰበከላቸው ፤ አስተማራቸውም ፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም ከእርሱ ጋር ነበሩ ። ከክፉዎች አጋንንትና ከልዩ ልዩ ደዌያቸው ያዳናቸው ሴቶችም አብረውት ነበሩ ።

ሙሉዉን ንባብ ያንብቡ

መዝሙረ ዳዊት ፻፵፮:፰

ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል፤ ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል፤ ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም።

የሐዋርያት ሥራ ፳፭:፲፩-፳፩

፲፩ ከበደልኩ ለሞት የሚያበቃኝ የሠራሁት ክፉ ሥራ ካለም ሞት አይፈረድብኝ አልልም ፤ በደል የሌለኝን እሊህ በከንቱ የሚከስሱኝ ከሆነ ግን ፤ ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ ለማን ይቻለዋል ፤ እኔ ወደ ንጉሥ ቄሣር ይግባኝ ብያለሁ ።